=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
ፍትሃዊ መሆን አእምሮአዊና ሃይማኖታዊ ግዴታ ነው። ድንበር ማለፍም ሆነ ድርቅና ተፈላጊ ባህሪያት አይደሉም። ነገሮችን ከልክ ማሳነስም ሆነ ማስበለጥ አይወደድም። ደስታን የፈለገ ሰው ስሜቱን እና ግንፍልተኝነትን መቆጣጠር አለበት። በደስታውና በቁጣው ፤ በሀዘኑና በውዴታው ፍትሃውዊ መሆን አለበት። ምክኒያቱም ከችግሮች ጋር መጨናነቅና አለአግባብ መወራጨት ነፍስን መበደል ነው። ልከኛ መሆን ምንኛ ያማረ ነው። ኢስላማዊ ድንጋጌ በሚዛን ወረደ ፤ ህይወትም በፍትህ ቆመች። ከሁሉም የሰው ልጆች ደካማ ማለት ለስሜቱ እጅ ሰጥቶ ዝንባሌውን የተከተለ ነው። ይህ ሰው ይሄን በማድረጉ ጥቃቅን ጉዳቶችን ከመጠናቸው በላይ ቦታ ሰጥቶ ይጨነቅላቸዋል። በቀልቡም ውስጥ የምቀኝነት ፣ የጥላቻና የክፋት ጦርነቶች ይካሄዳሉ። ምክኒያቱም በብዥታና በጥርጣሬ ውስጥ ስለሚኖር። ሁሉም ሰው የሚቃረነው ፤ ሌሎች ደግሞ እሱን ለማጥፋት የሚያሴሩ ይመስለዋል። ጉትጎታውም ___ንያ በሄደበት ተከትላ እንደምታጠፋው ይደሰኩርለታል። ስለዚህ የፍራቻ ፣ ጭንቀትና ትካዜ ጠቇራ ደመና ውስጥ ይኖራል። ፅንፈኝነት በሸሪአው የተወገዘ በባህሪም የረከሰ ነው። የህያው እሴቶችና አምላካዊ የአኗኗር ሥርዓት ድሆችን እንጂ ማንም አያዘወትረውም።
ቀልብህን እዚያው ባለበት ዙፋኑ ላይ እንደተቀመጠ ተወው። ከሚፈሩ ነገሮች ብዙዎቹ አይከሰቱም። የምትሰጋው ነገር ካለ ከሚያስከታላቸው ጥፈፋቶች የከፋውን አስብና መቀበል እንዳለብህ ራስህን አሳምን። ያኔ ቀልብን ከሚበጣጥሱ በደለኛ ስጋቶች ነፃ ትሆናለህ።
ስለዚህ አንተ ብልህና አስተዋይ የሆንከው ለሁሉም ነገር የሚገባውን ክብደት ብቻ ስጠው። ነገሮችን ፣ ጉዳዮችንና ክስተቶችን አታክብዳቸው። ባይሆን ፍትሃዊ ሁን ፣ አታዳላ። ከብዥታና ከጥርጣሬ እንዲሁም ከአታላይ ጋር አትጓዝ። የውዴታና የጥላቻ መለኪያቸው ምን እንደሆነ በዚህ ሐዲስ ላይ ተመልከት:-
«ወዳጅህን ስትወድ ገደብ ይኑርህ ከእለታት አንድ ቀን ጠላትህ ሊሆን ይችላልና። ጠላትህንም ስትጠላ ገደብ ይኑርህ ከእለታት አንድ ቀን ወዳጅህ ሊሆን ይችላልና።»
--<({አል-ቁርአን 60:7})>--
«በናንተና በነዚያ ከነሱ ጋር በተጣላችሁት ሰዎች ጋር አሏህ መፋቀርን ሊያደርግ ይችላልአ አሏህም ቻይ ነው። አሏህም በጣም አዛኝ ነው።»
ብዙ ስጋቶችና ፍርሃቶች በምንም ላይ የተመሠረቱ ብዥታዎች ናቸው።
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|